የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የባአክሲዮኖች 27ኛ መደበኛ እና 14ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች ቅዳሜ ኀዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ አዲስ አበባ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል የሚካሄድ በመሆኑ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ተገኝታችሁ በጉባዔው ላይ እንድትሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡
1. የ27ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
1.1. የጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ፣
1.2. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፣
1.3. የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ. የ2022/2023 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣
1.4. የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ. የ2022/2023 የሒሳብ ዓመት ሪፖርት ማዳመጥ፣
1.5. በተራ ቁጥር 1.3 ላይ በቀረበው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
1.6. በተራ ቁጥር 1.4 ላይ በቀረበው የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
1.7. እ.ኤ.አ. በ2022/2023 የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ ውሳኔ መስጠት፣
1.8. እ.ኤ.አ. የ2022/2023 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ክፍያን መወሰን፣
1.9. እ.ኤ.አ. የ2023/2024 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ የአበል ክፍያ መወሰን፣
1.10. እ.ኤ.አ. የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን መሾምና የአገልግሎት ክፍያቸውን መወሰን፣
1.11. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ ሪፖርት ማዳመጥና ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት የሚያገለግሉ የቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን፣
1.12. ለአስመራጭ ኮሚቴ አባላት የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፣
2. የ14ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
2.1. የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በዳይሬክተሮች ቦርድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
2.2. በአዲሱ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 መሠረት የተሻሻለውን የባንኩን ረቂቅ የመመሥረቻ ጽሑፍ መርምሮ ማጽደቅ፣
3. ማሳሰቢያ
3.1. ጉባዔዎቹ ላይ የሚገኙ ባለአክሲዮኖች ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳላቸው ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የመጠቀሚያ ጊዜው ያላለፈበት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
3.2. በጉባዔዎቹ ላይ በግንባር ለመገኘት የማይችሉ ከሆነ በወኪልዎ አማካኝነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ለዚህም፡-
3.2.1. ጉባዔዎቹ ከሚካሄዱበት ከሦስት የሥራ ቀናት በፊት ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት 8ኛ ፎቅ አክሲዮንና ኢንቨስትመንት ክፍል ቀርበው ለዚሁ ዓላማ ባንኩ ያዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅጽ በመፈረም፣ ወይም
3.2.2. ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠና በጉባዔዎቹ ለመካፈል የሚያስችል የውክልና ሥልጣን የተሰጣቸው ወኪልዎ በዕለቱ በጉባዔዎቹ ቦታ የውክልና ሠነዱን ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ጉባዔዎቹን መሳተፍ ይችላሉ፡፡
3.3. ባለአክሲዮኖች የባንኩን ረቂቅ የመመሥረቻ ጽሑፍ ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ አክሲዮንና ኢንቨስትመንት ክፍል ቀርበው ኮፒውን በመውሰድ ወይም በባንኩ ድረ-ገጽ www.bankofabyssinia.com ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ
Leave a Reply