ታላቅ የምሥራች፣ ከአቢሲንያ ባንክ!

ታላቅ የምሥራች፣ ከአቢሲንያ ባንክ!

በባንክ ቴክኖሎጂ ፈር ቀዳጅ የሆነው አቢሲንያ ባንክ ዛሬም በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ፈጣን የቪዛ ካርድ ህትመት አገልግሎት እንዲሁም የዲጂታል ቪዛ ካርድ አገልግሎትን እነሆ ብሏል።

ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በዚህ ሰዓት እነዚህ አዳዲስ አገልግሎቶች  የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የኢኖቬሽን የሚኒስቴር ዴኤታ ዶር. ይሽሩ አለማየሁ በተገኙበት በብሔራዊ ሙዚየም በሚገኘው  የባንካችን ቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከል የምርቃት ሥነ ሥርዓቱ አየተካሄደ ይገኛል።

የፈጣን ቪዛ ካርድ ህትመት አገልግሎትን ለማግኘት፣ ደንበኞች ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልጋቸው  በአቅርቢያቸው ወደሚገኘውን የ ቨርቹዋል ባንኪንግ ሴንተር  በመሄድ የቪዛ ካርድ መጠየቅና ወዲያውኑ በስማቸው የተዘጋጀውን ካርድ  መረከብ ይችላሉ፡፡

ይህንን አገልግሎት ለባንኩ የቀድሞ ደንበኞች፣ ለአፖሎ ተጠቃሚዎች፣ ካርድ ለጠፋባችው፣ የምትክ ካርድ አገልግሎት እንዲሁም አዲስ አካውንት በቨርቹዋል ባንኪንግ ሴንተር ለሚክፍቱ ወዲያውኑ ካርድ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

አገልግሎቱን ልዩ የሚያደርገው

 • በኢትዮጵያ የመጀመሪያ መሆኑ

 • በቀን ለ24 ሰአት በሳምንት ለ 7 ቀናት የሚሰጥ መሆኑ

 • በካርዱ ወዲያውኑ   በ ATM እና POS   ላይ ግብይት መፈፀም መቻሉ

 ይህንን አገልግሎት በጀሞ፣ ብሄራዊ ሙዝየም፣ ጎፋ እና መሀል ሰሚት በሚገኙት ቨርቹዋል ባንኪንግ ሴንተሮቻችን ማግኘት እንደሚችሉ  እየገለጽን ባንካችን የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ወደ ሌሎቹ ቨርቹዋል ባንኪንግ ሴንተሮች የሚያስፋፋ ይሆናል፡፡ 

እንዲሁም የዲጂታል ቪዛ ካርድ አገልግሎት ለማግኘት ደንበኞች ስልካቸውን እንደ ATM ካርድ መገልገል የሚችሉ ሲሆን የአፖሎ መተግበሪያን በመጠቀም ቪዛ ካርዳቸውን ወደ ዲጂታል ቪዛ ካርድ በመቀየር ገንዘብ ከATM ለማውጣትም ሆነ POS ማሽኖች ላይ ለመክፈል ስልካቸውን ጠጋ በማድረግ መጠቀም ይችላሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button