bankofabyssinia.com

አቢሲንያ ባንክ ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረመ

አቢሲንያ ባንክ ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረመ

ባንካችን ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ሠነድ ሃገራችን ለዜጎች የብሔራዊ መታወቂያ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት አንድ አካል ሲሆን ፣በስምምነቱ መሠረትም ባንኩ የብሔራዊ መታወቂያ ለማግኘትና መረጃዎችን ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ለሆኑ ደንበኞችና ዜጎች ከፕሮግራም ቢሮ ጋር በማቀናጀት ተደራሽ የሆነ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ምዝገባው አስፈላጊ ዝግጅቶች ከተጠናቀቁ በኋላ በባንካችን ቅርንጫፎች እና ምቹ በሚሆኑ ቦታዎች ለባንካችን ተገልጋዮች እና በአጠቃላይ ለህብረተሰቡ ክፍት እንደሚሆን በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ባንኩንና ፕሮግራሙን በመወከል የተገኙ የሥራ ሃላፊዎች ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button