አቢሲንያ ባንክ በየአመቱ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ እንዲሁም የሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታት በያዝነው የአውሮፓውያን ወር ከማርች8-31, 2022 ድረስ በሁለት የተከፈሉ ውድድሮችን አዘጋጅቶ ለተሳታፊዎች ክፍት አድርጓል፡፡ እነርሱም፣ የመጀመሪያው የግጥምና የሙዚቃ ተሰጥኦ ውድድር ሲሆን ሁለተኛው የሴቶች የሥራ ፈጠራ ውድድር ነው፡፡
የግጥምና የሙዚቃ ውድድሩ ተሰጥኦ ያላቸውን ሴት ተሳታፊዎችን በማወዳደር በባለሙያና በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የህዝብ ድምጽ የተለዩ አሸናፊዎችን በየደረጃው የብር ሽልማት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ ሽልማቱም አንደኛ ለምትወጣው የብር 50000፣ ሁለተኛ ለምትወጣው የብር 30000 እንዲሁም ሶስተኛ ለምትወጣው የብር 20000 ሽልማት መሆኑ ታውቋል፡፡
በዚህም መሠረት በመርሃ-ግብሩ መሳተፍ የሚፈልጉ ሴት ተወዳዳሪዎች አስቀድመው የአቢሲንያ ባንክ የፌስቡክ ገፅን https://www.facebook.com/BoAeth መቀላቀል ይኖርባችኋል፡፡ በመቀጠልም በሙዚቃው ዘርፍ ተሰጥኦየን ያሳያል የሚሉትን ከሶስት(3) ደቂቃ ያልበለጠ የሙዚቃ ሥራ ያለ ሙዚቃ መሣሪያ በቪዲዮ ሰርተው እንዲሁም በግጥም ዘርፍ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተሳታፊዎች ከ20 መሰመር ስንኝ ያልበለጠ ስለሴት ወይም ሴትነት የተዘጋጀ ግጥም ከዚህ በታች በተቀመጠው ኢ-ሜይል መላክ ይኖርባችኋል፡፡
Icantalentcom@bankofabyssinia.com
በተያያዘም በሁለተኛው የሥራ ፈጠራ ውድድር ባንኩ ካሉት 10 ዲስትሪክቶች ከእያንዳንዱ ሶስት(3) የሥራ ፈጣሪዎችን በአጠቃላይ 30 የሥራ ፈጣሪ ሴቶችን በመምረጥ በአነስተኛ የወለድ ምጣኔና ካለመያዣ እስከ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ) የብድር አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ ፍላጎቱ ያላቸውና መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሥራ ፈጣሪዎች አቅራቢያቸሁ ባሉ ቅርንጫፎችና የዲስትሪክት ፅ/ቤቶች በመቅረብ ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት10 ቀን 2014 ዓም. ባሉት ቀናት ብቻ በፁሑፍ ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በእዚህ አጋጣሚ ለሴቶች ደንበኞቻችን የተዘጋጁትን የመደበኛ አደይና የወለድ አልባ ዘሃራ አገልግሎቶችን በመጠቀም የተሻሉ ጥቅሞችን እንድታገኙ እንጋብዛለን፡፡ ዝርዝር የብድር እንዲሁም የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ለመመልከት ከታች የሚገኘውን አባር ይመልከቱ
መልካም የሴቶች ቀን!
Leave a Reply