bankofabyssinia.com

አቢሲንያ ባንክ የ6ኛውን የታማኝ ግብር ከፋዮች ሽልማት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

አቢሲንያ ባንክ የ6ኛውን የታማኝ ግብር ከፋዮች ሽልማት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

በሐገር አቀፍ ደረጃ ለ6ተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር ላይ የፕላቲኒየም ደረጃ ሽልማትን ባንካችን አቢሲንያ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተቀብሏል፡፡

በትላንትናው እለት በብሔራዊ ቤተ-መንግስት በተካሄደው ፕሮግራም ላይ 550 ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ያገኙ ሲሆን ግብር ከፋዮች በሀገር ውስጥ ገቢ በ12 እና በጉምሩክ በ7 የመምረጫ መስፈርቶች መሰረት ተመዝነው እውቅናው ተሰጥቷቸዋል፡፡ 

የአቢሲንያ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሂሳብ አስተዳደር  አቶ ደሳለኝ ይዘንጋው የባንኩን የፕላቲኒየም ደረጃ እውቅናና ሽልማት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተቀብለዋል ፡፡

#BankofAbyssinia #Ethiopia #Award #Tax #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button