በየዓመቱ የሚከበረው የፀረ ሙስና ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በሕብረት እንታገል”! በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ሲሆን፣ ባንካችን አቢሲንያም ቀኑን ምክንያት በማድረግ ሠራተኞች የሙስናና ብልሹ አሠራርን አስከፊ ገፅታ እንዲገነዘቡና ትርጉም ባለው መንገድ በተቋም እንዲሁም በየትኛውም ቦታ ለመታገል እንዲችሉ ግንዛቤ የሚፈጥር መርሐ ግብር አከናውኗል፡፡
ኅዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ለግማሽ ቀን በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በተካሄደው በዚሁ መርሐ ግብር ላይ፤ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች፣ የባንካችን የበላይ ሥራ አመራር፣ የሥራ አመራር አባላት እና ሠራተኞች በተገኙበት በተለያዩ አስተማሪና አዝናኝ ፕሮግራሞች ተከብሯል፡፡
Leave a Reply