መስከረም 2013 ዓ/ም ባንካችን አቢሲንያ ቨርቹዋል የባንክ ማዕከል አስመርቆ ያስጀመረው ፈር ቀዳጅ ቴክኖሎጂ እነሆ ቁጥሩን ወደ 30 ከፍ በማድረግ ለሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ ለባንክ ኢንዱስትሪው የመጀመሪያ የሆነውን ቴክኖሎጂ ከማስፋፋት እና ለደምበኞቹ ተደራሽ ከማድረግ አኳያ ግስጋሴውን ቀጥሏል፡፡
ባሳለፍነው ቅዳሜ የካቲት 09/2016 ዓ.ም በሀገራችን በሚገኙ ዋና ዋና የክልል ከተሞችና እንዲሁም የንግድ እንቅስቃሴውን ማሳለጥና ማዘመን ይቻል ዘንድ እነሆ በሀረር ከተማ ቦቴ አካባቢ በቁጥር 30ኛ የሆነውን የቨርቹዋል ማዕከላችን በይፋ ያስመረቅን ሲሆን በእለቱም የሀረር ከተማ መዘጋጃ ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ኤልያስ የኑስ እንዲሁም የስራ ባልደረቦቻቸው በመገኘት የቨርቹዋል ማዕከሉን መርቀው ከፍተዋል፡፡
አቶ ኤልያስ የኑስ በእለቱ ባስተላለፉት መልዕክት የባንኮች መሰል ቴክኖሎጂ መስፋፋት ለሀገር ኢኮኖሚ ከሚያርገው አስተዋፅኦ በዘለለ ከተሞች የሚያርጉትን የንግድ ልውውጥ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የዋጀ መሆኑ በመግለጽ የሀረር ከተማንም የንግድ እና የቱሪዝም ማዕከልን ለማስቀጠል የባንኮች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት አቶ ኤልያስ አቢሲንያ ባንክም ይህን በመገንዘብ በቴክኖሎጂ ላይ እያደረገ ያለው ፈር ቀዳጅ ሚና እና ባንኩ ለቴክኖሎጂ እየሰጠ ያለውን ትኩረት አድንቀዋል፡፡ በማዕከሉ ምርቃት እለት በባንካችን የድሬደዋ ዲስትሪክት ዳይሬክተር፤ የዲስትሪክቱ የስራ መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የሀረር ከተማ መዘጋጃ ቤት የስራ ሃላፊዎች፤ የተከበሩ ውድ ደንበኞቻን የተገኙ ሲሆን ባንካችንም በቅርቡ ተጨማሪ የቨርቹዋል ማዕከላትን ስራ ለማስጀመር ዝግጅቱን ጨርሶ ወደ ደንበኞቹ እንደሚያደርስ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
Leave a Reply