አሁንም ባንካችን የሀገር ባለውለታዋችን በስማቸው ቅርንጫፎችን በመሰየም እየዘከራቸው ይገኛል፡፡ ይህም ለሀገራችን ዘመን አይሽሬ አበርክቶ ያደረጉ ባለውለታዎች ስማቸውን እና መልካም ተግባራቸውን ለመዘከር እና ለቀጣዩ ትውልድ ለማሳወቅ እና ትምህርት እንዲሆን በማሰብ ነው፡፡ጥቂት_ስለ_ብ_ጄነራል_ለገሠ_ተፈራ የሱማሊያ መንግስት ኢትዮጵያን ወረረ፡፡ በወቅቱ የሱማሊያ ፕሬዝደንት ዚያድባሪ ኢትዮጵያን የወረረው፣ የደርግ መንግሥት በጦርነት በተጠመደበት ወቅት ነበረ፡፡ የተረጋጋ መንግሥት እያላት ኢትዮጵያን መውረር አጸፋው ከባድ እንደሆነ የተረዱት ጠላቶቻችን የእርስ በርስ ጦርነት መግባታችንን ተከትለው ወረሩን፡፡በቀላሉም እስከ ሐረር ድሬዳዋ ጠላት እየገሰገሰ ገባ፡፡ ጠላት ተደሰተ ፎከረ ኢትዮጵያን በእጄ አስገባሁ አለ፡፡ ጣሊያን ያልሆነለትን እኛ ኢትዮጵያንን አሸነፍን ብለው ጮቤ ረገጠ፡፡ ለወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት መንግስቱ ኃይለማሪም ሱማሊያ በውጭ ኃይሎች ታግዛ ኢትዮጵያን እንደወረረች አልፎ ተርፎም ድሬዳዋ እና ሐረር ወዘተ አከባቢዎች በጠላት ቁጥጥር ስር መውደቃቸው ተነገራቸው፡፡
የሰሜኑን የእርስ በርስ ጦርነት ትተው ጦራቸው ፊቱን ወደ ሱማሊያ እንዲያዞር አዘዙ፡፡ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሱማሊያ ተመሙ!! የኃይል አሰላለፉ ሲታይ የሱማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ የተሻለ ጦርና የጦር መሳሪያ ነበረው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም በአየር ኃይልም ከእጥፍ በላይ በሆነ ቁጥር ተዋጊ ጀቶች ነበራቸው፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በቁጥር ከነሱ በብዙ ከማነሱም በተጨማሪ ዘመናዊነታቸው ከነሱ ጋር መነጻጸር አይችልም፣ የጠላት ጀቶች ዘመናዊ ነበሩ፡፡የመንግስቱን ትዕዛዝ ተቀብለው ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ተነስተው የሱማሊያ ዘመናዊ ተዋጊ ጀቶች ጋር ከተፋጠጡት ፖይለቶች አንዱ ብ/ጄነራል ለገሠ ተፈራ ናቸው!! የሱማሊያ ጄቶች ምንም ቢዘምኑም በዝተው ሰማዩን ቢያጨናንቁትም እንደ ብ/ጄ ለገሠ ተፈራ ልብ ሊኖራቸው አልቻለም፡፡ ሰማዩን ያደጉበት መስክ አስመሰሉት፡፡ አልያዝ አልጨበጥ አሉ፡፡ ከየት መጡ ሳይባል የሱማሊያን የጦር ጀት ያጋዩአቸው ጀመር!! ከታች ላለው የእግረኛ ወታደር ባልታሰበ ፍጥነት ከእይታ ተሰውሮ የሱማሊያን የእግር ጦር መግቢያ እስከሚያጣ አጣደፉት፡፡ በቅጽበት ወደላይ ይሾሩና የኢትዮጵያ ወታደሮች በጠላት አየር እንዳይመቱ ፊት ለፊት ገጠሙአቸው፡፡
የሰማዩ አንበሳ ብ/ጄ ለገሠ ተፈራ 6ቱን ዘመናዊ የጠላት ተዋጊ አውሮፖላኖች ወደ አመድነት ቀየሩአቸው፡፡ የእግር ወታደሮች በሰማዩ ደጀናቸው ተበረታቱ ጠላት ላይ በረቱ፡፡ ብ/ጄነራሉ መች በዚህ ረኩ ለምን እዛው አገራቸው ገብቼ ሳይነሡ አልደቁሳቸውም ብለው የኢትዮጵያን ድንበር ለቀዉ ወደ ጠላት አገር ገቡ፡፡ ከብዙ ራዳሮች እየተሰወሩ የጠላትን ሰፈር እየደበደቡ ማምለጥ ቢችሉም በአንደኛው ተገኙና ተመቱ፡፡ ብ/ለጄ ለገሠ ተፈራ ግን ንቁ ነበሩና ጄታቸው ቢመታም በፖራሹት ወረዱ፡፡ የጠላት ወታደሮች ጠብቀው አሰሯቸው፡፡ ለ11 ዓመትም በእስር በእንግልት አሳለፉ፡፡ ሆኖም በ1981 ዓ.ም. በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረገው የእስረኛ ልውውጥ ስምምነት ሊፈቱ ችለዋል፡፡ ሊቀመንበር መንግሥቱም ጄነራል ለገሠን በከፍተኛ ወታደራዊ ስነ-ስርዓት ከተቀበሉአቸው በኋላ የሀገሪቱ የመጨረሻ ደረጃ ኒሻን የሆነውን “የህብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ” ሸልመዋአቸዋል፡፡ ከጄነራል ለገሰ ሌላ ይህንን ሜዳይ የተሸለሙት ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው (አንደኛው ሊቀመንበር መንግሥቱ ራሳቸው ሲሆኑ ሁለተኛው ብ/ጄነራል ተስፋዬ ሀብተማሪያም ናቸው)፡፡
የቅርንጫፉ_አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ላምበረት መናኸሪያ አ.አ. የካ ክ/ከተማ ወረዳ 09
source@wagsumgobezie
Leave a Reply