ባንካችን ከዚህ ቀደም በተከታታይ ዓመታት ሲሳተፍ እንደቆየው ሁሉ የ2016 ዓ/ም የክረምት ወራትን አስመልክቶም አገር በቀል ችግኞች እንዲተከሉ አደርጓል፡፡
የእሴቱ መገለጫ አንዱ የሆነውን ማኅበራዊ ኃላፊነት መወጣት በተለያዩ ኩነቶች ተግባራዊ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ዓላማቸውን ደግፎ አባል በመሆን የተለያዩ ድጋፎችን እና ዓመታዊ የአባልነት ክፍያ እየፈጸመ ከሚገኝባቸው ተቋማት መካከል ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከልና አረንጓዴነትን በማስፋፋት ምንጮችን እንዲጎለብቱ የማድረግ ሥራን አስቀድሞ የጀመረው የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር አንዱ ነው፡፡ ባንካችንም ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ የማኅበሩ አባል በመሆን አብሮ እየሠራ ይገኛል፡፡
በዛሬው እለት የተለያዩ የባንኩ የስራ ክፍሎች፤ ስራ አስኪጆች የቅርስ ባለአደራ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የተለያዩ 7 አይነት ሀገር በቀል የሆኑ ችግኞችን በመትከል ማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ላይ የሚገኝ ሲሆን ወደፊትም መሰል ተግባራት ላይ ተሳታፊነቱን አጠናቅሮ ይቀጥላል፡፡
Leave a Reply