አቢሲንያ ባንክ የአረፋ በዓልን አስመልክቶ ለአካል ጉዳተኞች ከፍተኛ ስጦታ አበረከተ

አቢሲንያ ባንክ የአረፋ በዓልን አስመልክቶ ለአካል ጉዳተኞች ከፍተኛ ስጦታ አበረከተ

አቢሲንያ-አሚን ወደ ህብረተሰቡ ከመቅረብና የማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አኳያ፣ እገዛው የሚያስፈልጋቸው ዋና ዋና የሚባሉ የማህበረሰቡ ሁነቶችን እየመረጠና በጥናት ላይ የተመረኮዘ እንቅስቃሴ እያደረገ ውጤታማ የሆነ ተግባር በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በዚሁ መሠረት፣ ባንካችን ከአል አማና የበጎ አድራጐት ድርጅት ጋር በመተባበርና በመንቀሳቀሻ እጦትና በአካል ጉዳት ምክንያት መስራት፣ የራሳቸውን የገቢ ምንጭ መፍጠር ብሎም ለሌሎች የሥራ ዕድል መፍጠር እየቻሉ በተፈጠረባቸው ውስንነት ይህን ማድረግ በተገደቡ ወገኖቻችን ዙሪያ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ መፍትሔ ይሆናል ብሎ ያመነበትን የዋጋ ግምቱ 200,000 /ብር ሁለት መቶ ሺህ/ የሆነ ዊልቼር የባንኩ የወለድ ነፃ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት በሆኑት በአቶ አብዱልቃድር ሬድዋን አማካኝነት በስጦታ አበርክቷል፡፡
ይኸ ስጦታ ከፍተኛ ራዕይ ያላቸውን የአካል ጉዳተኛ ወገኖች ወደ ምርታማነት ለማምጣት ትልቅ በር ከመክፈቱ ባሻገር ባንኩን ከማህበረሰቡ ፊት በሙሉ ልብ እንዲቆም የሚያደርገው ትልቅ ሥራ የተሰራበት ኩነት ነው፡፡ በተጨማሪም መርሐግብሩ ብዙ ተከታታዮች ባለው ሚዲያ ሽፋን የነበረውና ከማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትና አዎንታዊ ምላሽ ያተረፍንበትና ተግባር ሆኖ አልፏል፡፡

ፕሮግራሙን በዩቲዩብ ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=0eJQqpvCnjA

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button