አቢሲንያ ባንክ ከጥር 2020 (G.c) ጀምሮ በመላ አገሪቱ የኤጀንሲ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወቃል: በ ONPS/06/2023 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ እና የክፍያ ፈቃድ መሠረት ወኪል ኤጀንሲ ውል የሚቋርጥበት ምክንያቶች መካከል ወኪሉ የንግድ እንቅስቃሴን ሲያቆም እንዲሁም ለባንኩ (ለብራንቹ) የጽሁፍ ፈቃድ ውጭ ቦታውን ማዛወር ወይም መዝጋት እንደሆነ ይታወቃል፡፡በመሆኑም በተጠቀሱት መሰረታዊ ምክንያቶች ባንኩ በጠቅላላ ካሉት ወኪሎች መካከል14,297 እንቅስቃሴ ያቆሙ ወኪሎችን ዉል ማቋረጥ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘው ዉሉን ለማቋረጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል ።
የወኪል ዉል ማቋረጫ ሂደት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ መመሪያ (ቁ. ONPS/06/2023) በሰጠው ፈቃድ መሠረት የወኪሎች ዉል ከመቋረጡ በፊት ለኤጀንቶች ማሳወቅ ተገቢ እንደሆነ ይገልፃል ይህንንም መክንያት በማድረግ ባንኩ ለሚመለከታቸው ብራንቾች በደብዳቤ ቁ. መአዲ/696/16፣ አሳዉቆአል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ እንቅስቃሴ ያቆሙ ወኪሎች ስም ዝርዝር አውጥተናል፤ በዚህም መሰረት ስማቹ ከዚህ በታች የተጠቀሰ ወኪሎች ከባንኩ ጋር መቀጠል የምትፈልጉ ከሆነ በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ በአቅራቢያቸው የሚገኘውን ቅርንጫፍ ዘወትር በስራ ሰአት በመገኘት ውላቹን ማደስ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በኋላ በይፋ ዉል የምናቋርጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
Leave a Reply