የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ እና 15ኛ አስቸኳይ ጉባዔዎች

የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ እና 15ኛ አስቸኳይ ጉባዔዎች

የተከበራችሁ የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ባአክሲዮኖች

በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366(1)፣ 367(1) እና አንቀጽ 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ የተሻሻለው የመመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 20 መሠረት የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 28 መደበኛ እና 15 አስቸኳይ ጉባዔዎች ሐሙስ ኅዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ አዲስ አበባ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባዔዎቹ ላይ እንድትገኙልን የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

  • የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07፣ የቤ/ቁ. 351/1
  • የባንኩ ዌብ ሳይት፡- https://www.bankofabyssinia.com
  • የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡- አቢሲንያ ባንክ አ.ማ.
  • የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር KK/AA/2/0001775/2004
  • የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት፡- በባንክ ሥራ ላይ የተሠማራ
  • አክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ፡- 15,000,000,000
  • አክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ፡- 14,209,349,000

1. የ28ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

1.1.   አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፣

1.2.   የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ. የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣

1.3.   የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ. የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት ሪፖርት ማዳመጥ፣

1.4.   በተራ ቁጥር 1.2 ላይ በቀረበው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

1.5.   በተራ ቁጥር 1.3 ላይ በቀረበው የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

1.6.   እ.ኤ.አ. በ2023/2024 የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ ውሳኔ መስጠት፣

1.7.   እ.ኤ.አ. የ2024/2025 የሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን መሾምና የአገልግሎት ክፍያቸውን መወሰን፣

1.8.   እ.ኤ.አ. የ2023/2024 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ክፍያን መወሰን፣

1.9.   እ.ኤ.አ. የ2024/2025 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ የአበል ክፍያ መወሰን፣

2. የ15ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

2.1.   የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በዳይሬክተሮች ቦርድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

2.2.   የባንኩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፣

3. ማሳሰቢያ

3.1. በጉባዔው መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻቸው ሥልጣን ባለው የመንግሥት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሠነድ ዋናውና ፎቶኮፒ በመያዝ ወይም በን/ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከ3 የሥራ ቀናት በፊት ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ አክሲዮንና ኢንቨስትመንት ክፍል ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማናቸውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

3.2.  በብሔራዊ ባንክ መመሪያ SBB/91/2024 መሠረት የባንኩ ቦርድ አባል እና ማንኛውም የባንኩ ሰራተኞች ከባለአክሲዮኖች ውክልና መቀበል አይችሉም፡፡

3.3. የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውና ኮፒውን በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፤ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

   የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button