ባንካችን አቢሲንያ ከታህሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ለስምንት ወራት የቆየ የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ የተዘጋጀ “የእንሸልምዎ” የሽልማት መርሐ ግብር ለሦስተኛ ጊዜ፤ እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ የማሰባሰብ “መቆጠብ ያሸልማል” መርሐ ግብርን ለሁለተኛ ጊዜ አከናውኖ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል ፡፡
ከ 95,000 በላይ የዕድል ቁጥሮችን የያዘው የ”እንሸልምዎ” መርሐ ግብር እና ከ 5.6 ሚሊዮን በላይ የእድል ቁጥሮችን የያዘው “መቆጠብ ያሸልማል” የተሰኝው መርሐ ግብር ባለ እድለኞችን ለመለየት መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም. በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዶ ባለ እድለኞች ተለይተው ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡ ስለሂደቱና ሽላማቱ ስለፈጠረባቸው ስሜት ተሸላሚዎቹ የሠጡትን ምስክርነት መስፈንጠሪያውን በመጠቀም ይመልከቱ፡፡
Leave a Reply