አቢሲንያ ባንክ በአቢሲንያ አሚን በኩል ለሁለተኛ ጊዜ ልዩ የስራ ፈጠራ ሀሳብ እና ክህሎት ላላቸው ሁሉ የተዘጋጀ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እስከ ብር 1,000,000 /አንድ ሚሊዮን ብር/ የሚያሸልም አሚን አዋርድ የተሰኘ የስራ ፈጠራ ውድድር ይዞ ቀርቧል፡፡
ውድድሩ የሚካሄደው በአዲስ አበባ እንዲሁም በደሴ እና በድሬዳዋ ከተሞች (የመጀመሪያ ዙር ውድድር ብቻ) ሲሆን በመላው አገሪቱ ፍላጐቱ ያላቸው ተወዳዳሪዎች በሚከተሉት አድራሻዎች ተገኝተው መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- ከአዲስ አበባ ውጭ /በክልል/ የሚገኙ ተወዳዳሪዎች፡ በአቅራቢያቸው በሚገኙ የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፎች ቀርበው መመዝገብ ይችላሉ፣
- በአዲስ አበባ የሚገኙ ተወዳዳሪዎች በባንኩ ዲስትሪክቶች በኩል ማለትም
1ኛ) ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት
ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንጻ ነጩ አፓርትመንት ያለበት ወይም አቢሲንያ ባንክ ሜክሲኮ ቅርንጫፍ (2ኛ ፎቅ)
ስልክ ቁጥር 0911- 88-82-57 (አቶ ሰይድ ኡመር)
0115-58-69-61
0115-58-66-60
2ኛ) ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት
ኤድናሞል አደባባይ መድኃኒዓለም ሞል አጠገብ አቢሲንያ ባንክ ቴሌ መድኃኒዓለም ቅርንጫፍ (1ኛ ፎቅ)
ስልክ ቁጥር 0905-68-71-72 (ወ/ሮ ሀና ሳሙኤል)
0116-67-09-55
0116-67-97-74
3ኛ) ማዕከላዊ አዲስ አበባ ዲስትሪክት
በቅሎ ቤት አካባቢ ግሎባል (ኢትዮጵያ) ሆቴል ፊት ለፊት ኒኮር ፕላዛ ህንጻ (5ኛ ፎቅ)
ስልክ ቁጥር 0926-20-11-15 (አቶ ሙሉቀን አውራሪስ)
0114-70-61-42
ከተወዳዳሪዎች የሚጠበቁ ዝርዝር መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- አመልካቾች በአካል መቅረብ ይኖርባቸዋል በውክልና መስተናገድ አይችሉም፡፡
- አመልካቾች የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ፣ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁበት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ የትምህርት ማስረጃ እና አንድ ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አመልካቾች ምክረ ሀሳባቸውን በወረቀት እንዲሁም በሶፍት ኮፒ /በሲዲ/ በማቅረብ መመዝገብ የሚችሉ ይሆናል፡፡
- አመልካቾች የአቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎጽ ደንበኞች መሆን ይኖርባቸዋል ካልሆኑም በሚመዘገቡበት ወቅት ሂሳብ መክፈት ይኖርባቸዋል፡፡
- አመልካቾች የሚያመጣቸው የፈጠራ ሀሳቦች ከሸሪዓው መርህ ጋር የሚቃረን አለመሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አመልካቾች ለፈጠራ ሀሳባቸው የፈጠራ ሀሳብ ባለቤትነት /patent right/ ያላቸው ከሆነ ኮፒ አድርገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አመልካቾች ከዚህ በፊት በሌሎች ውድድሮች ከተሳተፉና አሸናፊ ከሆኑ በዚህ ውድድር ላይ በተመሳሳይ ሀሳብ መሳተፍ አይችሉም፡፡
- ተወዳዳሪዎች በአንደኛ ዙር አሚን አዋርድ ውድድር ላይ ተሳታፊ ከነበሩ በሁለተኛው ውድድር ላይ መሳተፍ አይችሉም፡፡
- ተወዳዳሪዎች በግሩፕም ይሁን በተናጠል የሰሩትን የስራ የፈጠራ ሀሳብ ይዘው መቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ንድፈ ሀሳባቸውን ይዘው የሚቀርቡት ባንኩ አዘጋጅቶ በዌብሳይት እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ባስቀመጠው የንድፈ ሀሳብ ማዘጋጃ እቅድ(Template) መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት አላቸው
አቢሲንያ አሚን
እሴትዎን ያከበረ
Leave a Reply