ባንካችን አቢሲንያ 28ኛመደበኛ እና 15ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አከናወነ!

ባንካችን አቢሲንያ 28ኛመደበኛ እና 15ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አከናወነ!

ሐሙስ፤ ኅዳር 05/2017 ዓ.ም  በአዲስ አበባ ከተማ በኢንተርሌክዥሪ ሆቴል በተካሄደው28ኛው መደበኛው እና 15ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ  መከናወኑን ተከትሎ ባንኩ በአጠቃላይ ሀብት፤ በተቀማጭ ገንዘብ፤ በአጠቃላይ ገቢ እንዲሁም በደምበኞች ቁጥር ዕድገት ማስመዝገቡን አስታውቋል፡፡

በዕለቱ  በተከናወነው የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ላይ ባንካችን አቢሲንያ አጠቃላይ ሃብቱ 222.30 ቢሊየን ብር መድረሱ የተገለጸ ሲሆን ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የብር 32.79 ቢሊዮን ወይም የ 17.30 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተወስቷል፡፡

በበጀት አመቱ ባንኩ እንደ ቀደሙት አመታት ሁሉ በ2023/24 የተቀማጭ ገንዘብ ዕድገቱን አስጠብቆ የቆየ ሲሆን አጠቃላይ የተቀማጭ ሀብቱን ከ ብር 158.54 ቢሊዮን ወደ ብር 192.51 ቢሊዮን በማድረስ የ ብር 33.97 ቢሊዮን ብር ወይም የ 21.43 መቶኛ እድገት በማስመዝገብ የተቀማጭ  ገንዘብ እንዳይዋዥቅ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል ሲሉ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አዕምሮ በለጠ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ባንካችን  ጠቅላላ ገቢውን በማሳደግ የብር 27.75 ቢሊዮን መድረሱንና ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅትጋር ሲነፃፀር  የ 22.09 በመቶ እድገት ማሳየቱ እና ከታክስ በፊት ያለውን ትርፉን ብር5.28 ቢሊዮን  በማድረስ ባለፈው አመት ካስመዘገበው በ0.92% ማሳደጉ  የተወሳ ሲሆን  የደምበኞቹንም ቁጥር ማደጉን እንዲሁም ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ ተደራሽነት በማስፋት 69 (ስልሳዘጠኝ) የሚሆኑ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ አገልግሎትን ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎችንመክፈቱን በጉባዔው ወቅት ላይ ተወስቷል፤፤

በተጨማሪም ዘመኑ የሚጠይቀውን የዲጂታል ባንኪንግ እና የመረጃ ቴክኖሎጂ ግንባታ ባለፉት አመታት ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚያስችሉ፤ ተወዳዳሪነቱን የሚያጠናክሩ ደህንነትን ማዕከል ያደረጉ እና ለደምበኞች ችግር መፍትሄ ያበጁ በርካታ የባንክ የቴክኖሎጂ አማራጮችን ወደ ስራ ማስገባቱን የባንኩ ምክትል  ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አዕምሮ በለጠ አስታውቀዋል፡፡

የአቢሲንያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ በበኩላቸው ያለፈው ዓመት ምንም እንኳን የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ባንኩ ይህን ተቋቁሞ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቁመው ለሚቀጥለው በጀት አመት ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እርሳቸውና መላው የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ሠራተኛው ጨምሮ  ቁርጠኛ መሆናቸውን አውስተዋል፡፡

ባንኩ በአሁኑ ወቅትም የደምበኞቹ ቁጥር ከ 14 ሚሊየን በላይ መድረሱን ያስታወሰ ሲሆን  ካፒታሉንም ከ ብር 15 ቢሊየን ወደ 17.5 ቢሊዪን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑንና በተያያዥ ጉዳዮች፤ ባንኩ ጠንካራ ጎኑን በማጎልበት መሻሻል ባለባቸው አፈፃፀሞች ላይ ከባለአክሲዮኖች ጋር በሰፊው በመወያየት ስብሰባውን  አጠናቋል፡፡

ባንካችን ከዚህ ቀደም አስቀምጦት የነበረውን የ 5 አመት የስትራቴጂ ትግበራን  አጠናቆ አዲስ የስትራቴጂ ዘመን መጀመሩን ተከትሎ በቁልፍ አፈፃፀሞች  እጅግ የላቀ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን  የተጠናቀቀው የስትራቴጂ ዘመን ከመጀመሩ በፊት የደምበኞቹን ቁጥር ከ 1 ሚሊዮን ወደ 14 ሚሊዮን ያሳደገ ፤ የተቀማጭ ሀብቱን ከ 30 ቢሊዮን ወደ 200 ቢሊዮን የተሻገረ እንዲሁም  በኢትዮጵያ የባንኮች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈር ቀዳጅና ግንባር ቀደም የሆነባቸው የቴክኖሎጂ አገልግሎቱን ለደምበኞቹ ያበረከተበት ዘመን ሲሆን ለምሳሌ ያክል እንደ ቨርቹዋል ማዕከላትን ከማድረስ ጀምሮ (Instant Card Issuance) ካርዶችን ለተጠቃሚው በጠየቁበት ቅፅበት እስከመስጠት የደረሰ ቴክኖሎጂን ያበረከተበት የስራቴጂ ዘመን ሆኖ የተጠናቀቀበት፤ በተጨማሪም የተደራሽነቱን መጠን ለማስፋት በስትራቴጂው ዘመን የነበሩትን የቅርንጫፎቹን ቁጥር 331 የነበሩትን አሁን የተደራሽነቱን መጠን በመላው ሀገሪቱ በማስፋት ከ 900 በላይ ቅርንጫፎችን ወደ ስራ ማስገባት የቻለ ባንክ ሲሆን በአዲሱም የስትራቴጂ ዘመን የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን በማጠናከር አዳዲስ ምርትና አገልገሎቱን በመጨመር ለደምበኞቻችን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button