…. አለማውጣት በለሲቱን እንደመቅጠፍ፤
አባቶቻችን “ዕፀ በለስ በልቷል ብሎ አዳምን መውቀስ አይቻልም” ይላሉ፡፡ ለምን ቢሉ፣ አዳም በለስን መብላቱ ተገዶ አይደለም፤ ትእዛዝ ነው ያላከበረው፡፡ ትእዛዙ ምንድር ነው ቢሉ፣ “በለስን አትብላ! ከበላህ ትሞታለህ፣ ካልበላህ ግን ሺህ ዓመት እየታደስህ ለዘለዓለም ትኖራለህ….!” የሚል ነው፡፡ ዐሥራት በኵራትን አለማውጣት ደግሞ ዕፀ በለስ እንደመብላት ይቆጠራል፤ እንዴት ቢሉ፣ ከፈጣሪ የተሰጠ ትእዛዝ ነውና፡፡ ዐሥራት በኵራት ካወጣህ እጥፍ እያረግኹ እመልስልሃለው፤ ካላወጣህ ግን በቀዳዳ ኪስህ ትከታለህ አለ፡ ስለዚህ ዐሥራት በኵራት አለማውጣት በለሲቱን እንደመቅጠፍ ነው፡፡
ጥንተ ነገር ዘዐሥራት በኵራት
ዐሥራት፣ ሰው ከሚያገኘው ገቢ ኹሉ ከ፲ አንዱን ለእግዚአብሔር የሚያበረክተው ገጸ በረከት፣ አምሃ፣ እጅ መንሻ ማለት ነው፡፡ በኵራት ደግሞ ሰው ዘርቶ ካመረተው፣ ተክሎ ካፈራው፣ ከሚወልዳቸው ልጆችና ካረባው እንሰሳ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር መስጠት፣ መቀደስ ነው፡፡ ዐሥራት በኵራት ለፈጣሪ የሚበረከተው አምላክ ትእዛዝ በመኾኑ ነው፡፡ “የምድርም ዐሥራት ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ ቢኾን የእግዚአብሔር ነው፣…. ሰውም ዐሥራቱን ሊቤዥ (ቢያወጣ) ዐምስተኛ ይጨመርለታል፡፡ ከበሬውም ኹሉ ከአንድ ዐሥረኛውም በትር በታች ከሚያልፍ በግና ፍየል ኹሉ ከዐሥር አንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው፡፡” (ዘሌ. ፳፯÷፴-፴፫)፤ “ከእስራኤል ልጆች ከሰውም ከእንስሳም ማኅጸን የሚከፍት በኵር ኹሉ ለእኔ ይቀድስልኝ፣ የእኔ ነው፤” እንዲል፤ (ዘጸ. ፲፫÷፪)፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ዐሥራት ያወጣው አቤል ነው፤ ከእርሱ ቀጥሎ አብርሃምን እናገኛለን፡፡ አብርሃም ጠላቶቹን ድል አድርጎ ሲመለስ፤ መልከ ጼዴቅ መንገድ ላይ ጠብቆ ባረከው፤ ዐሥራት ሰጠው፤ ያዕቆብም “ከሰጠኸኝ ሁሉ ላንተ ከ፲ እጅ አንዱን እሰጣለሁ፤” ሲል በተሣለው መሠረት ለእግዚአብሔር ዐሥራት አውጥቷል (ዘፍ. ፳፰÷፳፪)፡፡ በዚኽ ጊዜ እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከው፣ እሥራኤል ብሎ ጠራው፡፡ በዛን ዘመን ታቦተ ጽዮን የሚገኝበትን ድንኳን የሚሠራው ከዐሥራት በሚወጣው ገንዘብ ነበር፣ ለመንፈሳዊ መገልገያ የሚኾኑት ዕጣን ዘይት መብራት.. ወዘተ. ሰዎች በሚያስገቡት መባ ነበር፡፡ (ዘጸ. ፳፭÷፫)
ዐሥራት በኵራት በኢትዮጵያ
ሕገ ልቡናን፣ ብሉይና ሐዲስ አስማምታ እግዚአብሔርን የምታመልከው ኢትዮጵያ፣ በአብርሃምና በያዕቆብ የተጀመረው ዐሥራት በኵራት የማውጣት ሥርዐትን ባህሏ አድርጋ ለዘመናት ስትፈጽም ኖራለች፡፡ ሕዝቧም የመጀመሪያ ወንድ ልጃቸውን ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግል አራት ዓመት ሲሞላው ለቤተ ክርስቲያን ያስረክቡ ነበር፡፡ የቀደሙት ነገሥታት፣ ባላባቱና መኳንንቱም የአገርን ድንበር ለሚድፈርና ሃይማኖትን ለማጥፋት የሚመጣውን ጠላት ድል አድርገው ከሚማርኩት ንብረት ከ፲ እጅ አንዱን ያስገቡ ነበር፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት የተገነቡትና ዛሬ ላይ በታላላቅ ገዳማትና አድባራት የምናገኛቸው ቅርሶች የተበረከቱት ከዘመቻ መልስ ነበር፡፡ ዐፄ ገላውዴዎስ ተድባበ ማርያምን የገነቡት ግራኝን ድል አድርገው ከተመለሱ በኋላ በገቡት ቃል ኪዳን መሠረት ነው፤ አራዳው ጊዮርጊስን ዐፄ ምኒልክ ያስገነቡት ከዐድዋ ድል በኋላ ነው፤ ምስካየ ኅዙናን መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ዐፄ ኀይለ ሥላሴ ከጣሊያን ወረራ በኋላ አገሬን ከጠበክልኝ መቅደስህን እሠራለው ባሉት መሠረት የተገነባ ነው፡፡
የቀደሙቱ የራሳቸውን ጎጆ ከመሥራታቸውም በፊት የእግዚአብሔርን ቤት ነበር የሚያንጹት፤ ይኽ በማድረጋቸው በረከትን፣ ምሕረትን አግኝተውበታል፡፡ ስንቶቻችን ዐሥራት በኵራትን እያወጣን ቃሉን ፈጽመናል? ይኽን ትእዛዝ የማንፈጽም ደግሞ እግዚአብሔርን መስረቅ ነው፡፡
“ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል፡፡ እናንተም የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል፡፡ በዐሥራት በኵራት ነው” ይላልና፡፡ (ትንቢተ ሚልኪያስ ፫÷፰)
ዛሬ ላይ በዚኽ ሩጫ በበዛበት ዓለም ሃይማኖታዊና ባህላዊ ግዴታችንን ዘንግተን በከንቱ የባዘንን ሞልተናል፡፡ አልሞላ እያለን በጎተራ የምናስቀምጠው ጥሪት እንደተበሳ ከረጢት እየፈሰሰ በረከትን አጥተን ትርፋችንን ድካም ታቅፈናል፡፡ በመፈለግ ውስጥ አለማድረግ፣ ባለማድረግ ውስጥ አለመባረክ፤ ትእዛዙን ባለመፈጸም በለሲቱን እየቀጠፍን እንገኛለን፡፡ ብዙዎቻችን ዐሥራት በኵራትን ለመውጣት ብናስብም ወደ መሬት አውርደን መተግበር ያቅተናል፡፡ አንዳንዶቻችን ደግሞ ለዐሥራት በኵራትያስቀመጥነውን ገንዘብ እንዴት ላለ መንፈሳዊ ሥራ ላይ ማዋል እንዳለብን ይቸግረናል፡፡ በጊዜ መጣበብ ምክንያት የማናወጣም እንገኛለን፡፡ ታዲያ መቼና እንዴት ባለ ዘመናዊ መንገድ ሃይማታዊ ግዴታችን የምንወጣው የሚለው ጥያቄ በቶሎ መልስ ያሻዋል፡፡
ለዚኽ ኹሉ ችግራችን መፍትሔ የሚሰጠን፣ ለተቀደሰው ዐላማ ሓላፊነትን ወስዶ ዘወትር የሚቀሰቅሰን፣ ግዴታችንን በመወጣ በረከትን እንድንጎናጸፍ የሚረዳን አካል ማግኘት ይገባናል፡፡
እነኾ! አቢሲንያ እርስዎ ሩጫዎትን ሳያቋርጡ ሀብትዎን የመባረኪያ መንገድ፣ ዐሥራት በኵራት የተሰኘ ልዩ አገልግሎት አቀረበልዎ፡፡ አቢሲንያ ባንክ ያለብንን ሃይማኖታዊ ግዴታ እያስታወሰ በየወሩ ዐሥራታችንን እንድናወጣ ያቀረበልን ዐሥራት በኲራት ልዩ የሒሳብ ደብተር። የቄሳርን ለቄሳር እንዲሉ በዚኽ የሒሳብ ደብተር ከደመወዝዎ የሚያገኙትን ገንዘብ ለሚፈልጉት መንፈሳዊ ዐላማ እንዲያወሉ በሚያስችል መንገድ የቀረበ ምርጥ መፍትሔ ኾኖ ተገኝቷል፡፡ በሚከፍቱት የዐሥራት በኵራትየተቀማጭ ሒሳብ በየወሩ ባንካችን ለሚፈልጉት ቤተ ክርስቲያን፣ ገዳማትና ወአድባራት ገቢ ያደርጋል፣ ድጋፍ ለሚያደርጉት የተለያዩ መንፈሳዊ ፕሮጀክቶች ገንዘብዎን ይልካል፡፡ እርሶ ከዚኽ በኋላ ስለ ሥራዎ ይጨነቁ፤ እኛ አቢሲንያ ደግሞ ስለገንዘብዎ እንጨነቃለን፡፡
የዐሥራት በኲራት ሒሳብ መለያዎች
- ለቁጠባ ሒሳብ የሚከፈለውን የወለድ ተመን ያስገኛል፤
- ሒሳቡ በጋራ ወይንም በድርጅት ስም ለዐሥራት በኲራት ተብሎ በተለየ ሒሳብ መከፈት ይችላል፤
- ወጪ/ገቢ ማድረግ ሲፈለግ በማንኛውም ጊዜ በዲጂታል አገልግሎቶች ወይም ወጭ/ገቢ ማዘዣ ቅፅ ወጪ/ገቢ ማድረግ ይቻላል፤
- ለሒሳብ መክፈቻ የሚያስፈልገው መነሻ ብር ፶ (ሃምሳ ብር) ይኾናል::
አገልግሎቱ የሚያስገኛቸው ልዩ ጥቅሞች፤
- የሒሳብ ባለቤቶችን በተመለከተ፤
- ዐሥራት በኲራት ሒሳብ የከፈተ ደንበኛ በቋሚ ትእዛዝ ከሌላ ሒሳቡ እንዲቀነስ ወይም በዐሥራት በኲራት ከተቆጠበው ላይ ተቀንሶ ለተጠቃሚ እንዲተላለፍለት ሲያዝ ያለ ክፍያ ይስተናገዳል፤
- ደንበኛው የሰጠውን ቋሚ ትእዛዝ መቀየር ወይም ማስቆም በፈለገ ጊዜ ያለ ክፍያ ወዲያውኑ ይደረግለታል፤
- ደንበኛው በወር ፩ ጊዜ ከሒሳብ ወደ ሒሳብ ወይም በሐዋላ ለተጠቃሚ በነፃ ማስተላለፍ ይችላል፤
- የሒሳብ ዝርዝር መግለጫ ደንበኛው በመረጠው መንገድ (ኢ- ሜይል፣ ሶፍት ኮፒ/ ሃርድ ኮፒ) ሲያመለክት በወር ፩ ጊዜ ይሰጠዋል፣
- አብያተ ክርስቲያናት/ዐሥራት በኲራት ተቀባዮችን በተመለከተ፤
- የሒሳባቸውን መግለጫ በመረጡት መንገድ (ኢ-ሜይል፣ ሶፍት ኮፒ/ሃርድ ኮፒ) በማመልከት በወር ፩ ጊዜ ያለ አገልግሎት ክፍያ መውሰድ ይችላሉ፤
- ባንኩ በየአብያተ ክርስትያናቱ የተሰበሰበውን ጥሬ ገንዘብ በመረጡት ቀን ከቦታው በመሔድ ወደ ባንክ ያስገባል፤
- ባንኩ በልዩ ኹናቴ የተዘጋጀ ትልቅ ‹‹ሙዳይ አቢሲንያ›› ሳጥን ለአብያተ ክርስትያናቱ ያበረክታል።
ምኒልክ ብርሃኑ
Leave a Reply