ውድ ደንበኞቻችን! ባንካችን አቢሲንያ ከውጪ ሀገር የተላከ ገንዘብን በባንካችን ለሚቀበሉ እና ለሚመነዝሩ “እንሸልምዎ” እንዲሁም ገንዘብ በባንካችን ለሚቆጥቡ “መቆጠብ ያሸልማል” በተባሉ ሁለት የሎተሪ ሽልማት መርሐግብሮች በተለየዩ ዙሮች በርካታ ዕድለኞችን እንደሸለመ ይታወቃል፡፡ አሁንም በልዩ ሁኔታ በሌላ ዙር ዕድለኞችን ለመሸለም እየተሰናዳ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እነኚህን ሽልማቶች የተሻሉ ለማድረግ እንዲረዳን፤ ይኽችን አነስተኛ መጠይቅ ካለዎት ውድ ጊዜዎ ላይ ጥቂት ለግሰው በአማርኛ...
Author: Bank of Abyssinia (Bank of Abyssinia )
ማኅበራዊ ኃላፊነት ተፈጥሮአዊ ዕሴታችን፤
እንደ ሐረግ ለተጠላለፈው ኢትዮጵያዊ ማንነት፤ ክሩም፣ ማጉም አንድ ነው፡፡ በዚህ የአንድነት ማግ የተጠናከረው ኢትዮጵያዊነት፤ ዛሬ ያልተጀመሩ፣ በነገ የማይጠናቀቁ የብዙ ትላንቶች ባለቤት እና በማይሰበር ዐለት ላይ የተዋቀረ “አገር” እንድንሆን አድርጎናል፡፡ በዚህ ዓምድ የተገነባው ባንካችን፣ የቀድሞውን የኢትዮጵያን ስም በመዋስ በታላቋ አገር ታላቅ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ከዛሬ 26 ዓመት በፊት “አቢሲንያ” በሚል ስም ተመሠረተ፡፡ መልካም ስም ከመልካም ተግባር...
በ “መቆጠብ ያሸልማል” እና የ“እንሸልምዎ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ!
አቢሲንያ ባንክ ደንበኞቹን ለማበረታታት የተለያዩ የሽልማት ስጦታዎችን እያዘጋጀ ከዘርፉም የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ እንደሆነ ይታወሳል፡፡ ዘንድሮም የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ የተዘጋጀ “የእንሸልምዎ” የሽልማት መርሐ ግብር ለአራተኛ ጊዜ፤ እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ የማሰባሰብ “መቆጠብ ያሸልማል” መርሐ ግብርን ለሦስተኛ ጊዜ ከታኅሣሥ 23 እስከ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አከናውኖ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሐምሌ 14...
፲ የፋይናንስ አቅማችንን የምናሳድግባቸው አማራጮች
ለአንድ የንግድ ድርጅት ጠንካራ ሥርዐትና (System) የሰው ኃይል የጀርባ አጥንት ሊሆን ይችላል። ግን የፋይናንስ ዐቅሙ የተዳከመ ከሆነ ከባድ የሕልውና ሥጋት ውስጥ ይወድቃል። በዚህ የውድድር ዓለም ውስጥ ለመዝለቅ፤ ተመራጭና ተፈላጊ ሆኖ ለመቆየት ግዴታ የገንዘብ ዐቅምን ማሳደግ ይገባል። የፋይናንስ ዐቅማችንን ከምናሳድግባቸው መንገዶች ብዙዎች የሚስማሙባቸውን እነሆ። ፩. የፋይናንስ እቅድ ያዘጋጁ፤ ፋይናንስን ለመቆጣጠርና ግቦችን ለማሳካት የፋይናንስ እቅድ አስፈላጊ ነው።...
አቢሲንያ ባንክ የአረፋ በዓልን አስመልክቶ ለአካል ጉዳተኞች ከፍተኛ ስጦታ አበረከተ
አቢሲንያ-አሚን ወደ ህብረተሰቡ ከመቅረብና የማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አኳያ፣ እገዛው የሚያስፈልጋቸው ዋና ዋና የሚባሉ የማህበረሰቡ ሁነቶችን እየመረጠና በጥናት ላይ የተመረኮዘ እንቅስቃሴ እያደረገ ውጤታማ የሆነ ተግባር በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡በዚሁ መሠረት፣ ባንካችን ከአል አማና የበጎ አድራጐት ድርጅት ጋር በመተባበርና በመንቀሳቀሻ እጦትና በአካል ጉዳት ምክንያት መስራት፣ የራሳቸውን የገቢ ምንጭ መፍጠር ብሎም ለሌሎች የሥራ ዕድል መፍጠር እየቻሉ በተፈጠረባቸው ውስንነት ይህን...
የዲጂታል ክፍያ አማራጮች ከጥሬ ገንዘብ ነጻ ለሆነ ማኅበረሰብ
(DIGITAL PAYMENT OPTIONS for CASHLESSS SOCIETY) ሁሉም የገንዘብ ልውውጦች በባህላዊ መንገድ በሚከናወኑበት ሁኔታ፤ ከጥሬ ገንዘብ ነጻ የሆነ ማኅበረሰብ ማግኘት ያስቸግራል፤ በተለይ ደግሞ ቴክኖሎጂ ባልተስፋፋባቸው አገራት። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ያሉ ግብይቶች የዲጂታል ክፍያዎችን በመከተላቸው፤ በጥሬ ገንዘብ መገበያየት ያለፈበት ፋሽን እየሆነ ነው። ከበይነ መረብ ጋር ተያይዞ የተፈጠሩት የዲጂታል ክፍያ ሥርዐቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ...
አሚን አዋርድ
አቢሲንያ ባንክ “አቢሲንያ አሚን” በሚል የሰየመው ከወለድ ነፃ አገልግሎቱ፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ ዕቅዶች ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህም አንዱ “አሚን አዋርድ” በሚል መጠሪያ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማትን የሚሰጥበት መርሐግብር ነው፡፡ ት/ቤቶች አምራች እና ብቁ ዜጎችን ከመፍጠር አኳያ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል ይህንን የትምህርት ቤቶችን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም የተማሪዎችን ተነሳሽነት እና...
የሞባይል ባንኪንግ ደኅንነት ምክሮች
ትላንት የባንክ አገልግሎት ጊዜ የሚወስድ ነበር። ዛሬ፣ ብዙ አማራጮች አሉን፤ አንደኛው የሞባይል ባንኪንግ ነው፡፡ ታዲያ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ደኅንነታቸው የተጠበቀ ነው? አዎ! የሞባይል ባንኪንግ ደኅንነቱ የተጠበቀ ብቻ ሳይሆን በጣም ምቹና ፈጣን፤ በየቅርንጫፎች በመሔድ የሚመጣውን መስተጓጎልን የሚያስወግድ፤ በቀላሉ ገንዘብዎን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር የሚመች መንገድ ነው። የሞባይል ባንኪንግ የተለያዩ የባንክ መተግበሪያዎችና ዘዴዎች በመኖራቸው ደኅንነቱ የተጠበቀ ነው። መተግበሪያን በሚጠቀሙበት...
አቢሲንያ ባንክ የ ብር 2 ሚሊየን ድጋፍ ለፓርትነርሽፕ ፎር ፓስቶራሊስት ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን ሰጠ፡፡
ባንካችን አቢሲንያ ፓርትነርሽፕ ፎር ፓሰቶራሊስት ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ሊበን ዞን የሚገኙ በድርቅ የተጎዱ 2 ወረዳዎችን መልሶ ለማቋቋም እየሠራ የሚገኘውን በጎ ተግባር ማገዝ ይቻል ዘንድ የብር 2 ሚሊዮን ድጋፍ አድርጓል፡፡ድጋፉን በማስመልከት የተሰናዳው ዝግጅትም ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በባንካችን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የባንኩ የሸሪአ ቦርድ አማካሪ የሆኑት ሀጂ ኑረዲን...
አቢሲንያ ባንክ በባንኪንግ ኢንደስትሪው ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነውን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞችን ያማከለ ቨርቸዋል የባንክ ማዕከል ሥራ አስጀመረ
ባንካችን የአምስት ዓመት የስትራቴጂ ዕቅዱን ሲነድፍ ለደንበኞች ምቾቱን የጠበቀና የላቀ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት በማሰብ ለዲጂታል ቴክኖሎጂ (Digitalization) ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አያሌ አበረታች ተግባራትን አከናውኗል፡፡ በዚህም መሠረት፣ ባንካችን በስልታዊ ዕቅዱ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ አቢሲንያ ኦንላይን፣ ኢ-ኮሜርስ ፔይመንት ጌትዌይን የመሳሰሉ የኦንላይን የባንክ አገልግሎቶችን በመጀመር፣ እንዲሁም የክፍያ ማለትም የኤ.ቲ.ኤምና የፖስ መሣሪያ በማኅበረሰባችን ዘንድ ይበልጥ ተደራሽ...