አቢሲንያ በአውታር የጥበብ ገበታ!

አቢሲንያ በአውታር የጥበብ ገበታ!

አቢሲንያ ባንክ የሀገራችን የሙዚቃ ጥበብ እንዲያድግ ካለው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ የኢትዮጵያ ሙዚቃ በየትኛውም የዓለማችን ጫፍ ባሉ የሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ተደራሽ መሆን የሚችልበትን የክፍያ ቴክኖሎጂ ዘርግቷል፡፡ከእንግዲህ ወዲያ የሀገራችን ሙዚቀኞች ሥራቸውን ለዓለም ገበያ አውታር በተሰኘው የሙዚቃ መተግበሪያ በኩል ለሽያጭ ሲያቀርቡ አቢሲንያ ባንክ የክፍያውን መንገድ በማመቻቸት ከጎናችሁ ነን ይላል፡፡ በየትኛውም የዓለማችን ጫፍ ያለ የሙዚቃ አፍቃሪ የቪዛ እና ማስተር ካርዱን በመጠቀም የፈለገውን ሙዚቃ ቢያሻው በነጠላ (Single) ቢያሻው ሙሉ አልበም (Full Album) ከአውታር የሙዚቃ መተግበሪያ መግዛት ይችላል፡፡ባንካችን ለጥበብ ዕድገት የደረገው ድጋፍ በሀገራችን ካሉት የፋይናንስ ተቋማት ቀዳሚ የሚያደርገው ሲሆን፣ አገልግሎቱ ሙዚቃን በቀላሉ ማግኘትና መጠቀም የሚያስችል ነው፡፡ ሙዚቃ የሰው ልጅን ያህል እድሜ ያስቆጠረ ጥንታዊ የጥበብ ትሩፋት ነው፡፡ ስመ ጥሩ የሀገራችን ድምፃዊ ካሳ ተሠማ በግሩም ድምጹ ስለ ሙዚቃ የሚከተለውን አዚሟል፡-…….

ብስጭት፣ ጭቅጭቅ፣ ሀዘን ወይ ትካዜ፣

ይርቃሉ ከሰው አንቺ ባለሽ ጊዜ፡፡

ሰው ሀዘን ሲወረው ቸግሮት መሸሻ፣

አንቺ ነሽ ምሽጉ እስከ መጨረሻ፡፡

……..

ሥራሽ ተዘርዝሮ ብዙ ነው መች ያልቃል፣

ሙዚቃ ስሜት ነሽ ብንልሽ ይበቃል፡፡

………

ሁላችንም እንደምናስተውለው፣ የሀገራችን ሙዚቃ ከያኒውን ሲጠቅም በብዛት አይስተዋልም፡፡ ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት የቅጅ መብት በሚፈለገው ደረጃ አለመከበሩ ነው፡፡ በመሆኑም፣ ድምጻውያን ሙሉ የሙዚቃ አልበምን ከማውጣት እየራቁ፣ በአንጻሩ ነጠላ ሙዚቃዎችን ዩቲዩብን በመሰለ ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ ሲለቁ እና መጠነኛ ገቢ ሲያገኙ እናያለን፡አውታር መልቲሚዲያ በሙዚቀኞች የተመሠረተ፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሙዚቃ መሸጫ የስልክ መተግበሪያ አዘጋጅቶ የሙዚቃ አድናቂው የሚፈልገውን ሙዚቃ በቀላሉ፣ በፍጥነት እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ የሚያስችል እንዲሁም የሙዚቃ ባለሙያ የሠራውን ሥራ እንደ ሥራ ድርሻው ተጠቃሚ የሚያደርግ የሙዚቃ መገበያያ ሥርዓት በማስተዋወቅ፣ አደጋ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ሊታደግ በሚያስችል መልኩ የራሱን አሻራ በመጣል ሥራውን የጀመረ ተቋም ነው፡፡ዛሬም በአቢሲንያ ባንክ አማካኝነት በመላው ዓለም የሚገኙ የሙዚቃ አድናቂዎች የፈለጉትን ሙዚቃ ከአውታር የሙዚቃ መተግበሪያ ላይ በማስተር ካርድ እና በቪዛ ክፍያ በመፈፀም የሙዚቃ ግዢ የሚያደርጉበትን መንገድ አመቻችቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚሠሩ ሙዚቃዎች በትኩሱ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተደራሽ እንዲሆን በሚያስችል መልኩ ሥራ ጀምሯል፡፡

#E-Commerce #Visa #mastercard #awtarapp

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button