በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  • በተራ ቁጥር 2 (ሁለት) ላይ የተጠቀሰው ንብረት የተጨማሪ እሴት ታክስ አይከፈልበትም።
  • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 12 ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button