የዲጂታል ክፍያ አማራጮች ከጥሬ ገንዘብ ነጻ ለሆነ ማኅበረሰብ

የዲጂታል ክፍያ አማራጮች ከጥሬ ገንዘብ ነጻ ለሆነ ማኅበረሰብ

(DIGITAL PAYMENT OPTIONS for CASHLESSS SOCIETY)

ሁሉም የገንዘብ ልውውጦች በባህላዊ መንገድ በሚከናወኑበት ሁኔታ፤ ከጥሬ ገንዘብ ነጻ የሆነ ማኅበረሰብ ማግኘት ያስቸግራል፤ በተለይ ደግሞ ቴክኖሎጂ ባልተስፋፋባቸው አገራት። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ያሉ ግብይቶች የዲጂታል ክፍያዎችን በመከተላቸው፤ በጥሬ ገንዘብ መገበያየት ያለፈበት ፋሽን እየሆነ ነው።

ከበይነ መረብ ጋር ተያይዞ የተፈጠሩት የዲጂታል ክፍያ ሥርዐቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ መደበኛ አሠራር በመሸጋገራቸው በቅርብ ዓመታት ውስጥ ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል። በ1960ዎቹ ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ባንክ አገልግሎት መስጠት በተጀመረበት ጊዜ የተለመደው የዲጂታል ክፍያ፤ በአካላዊ የባንክ ኖቶች ሳይሆን በዲጂታል ወይም በኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ውክልና በመውሰድ የሚከወኑ ናቸው። በአሁኑ ሰዓትም፤ “ዲጂታል ክፍያዎችን መጠቀም አለብን ወይ” የሚለው ላይ ብቻ ሳይሆን “ክፍያዎችን በፍጥነት፣ በተሻለና ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዴት እንደምንፈጽም” ወደሚል ጥያቄ በመምጣቱ፤ ጥሬ ገንዘብ ወደማይጠቀም ማኅበረሰብ እየወሰደን ነው፡፡

የዲጂታል ክፍያ፤ የፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ውጤት ሲሆን፤ በየጊዜው እየሠለጠኑ ከመጡ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ ክፍያ (FinTech payment) ከሚባሉት ውስጥ ዋነኛው ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የባንኮች የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሒደት እየተስፋፋ በመምጣቱ የዲጂታል ምንዛሬዎች፣ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ክፍያዎች (FinTech payment) እየጨመረና ከዲጂታል ዓለም ጋር እየተጣጣመ በማደግ ላይ ይገኛል፡፡ እንደዚህ ዐይነት የክፍያ ቴክሎጆዎች በመስፋፋታቸው ከጥሬ ገንዘብ ነጻ የኾነ ማኅበረሰብ መፍጠር ተችሏል፡፡

አንዳንድ አገራት ሙሉ በሙሉ ጥሬ ገንዘብ የሌለው ማኅበረሰብ (CASHLESS SOCIETY) ለመሆን በጉዞው ላይ ናቸው። በዓለም ላይ 15 ጥሬ ገንዘብ አልባ አገራት ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ ስዊድን፣ ስዊዘርላንድ፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ እንግሊዝ፣ ኤዥያ፣ ሰሜን አሜሪካ ወዘተ… ፡፡ ይኽም የሚያሳየው ዓለም ከምንጊዜው በላይ ወደ ዲጂታል ሥርዐት እየተለወጠ መኾኑን ነው፡፡

ዛሬ የፋይናንሺያል ግብይቶች በኮምፒዩተርና ተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች በመሆናቸው በዓለም ዙሪያ የጥሬ ገንዘብ አጠቃቀም እየቀነሰ ነው፡፡ በዲጂታል መተግበሪያዎች መብዛት ክፍያዎችን ይበልጥ ምቹ፣ ግብይቶች ፈጣን፣ ከሰዎች ንክኪ ነጻና የተሻለ ገቢ ምምጣት ተችሏል፡፡ ምቹ፣ ፈጣንና ቀጥተኛ ክፍያዎችን መፈጸም በመቸሉም ከየትኛውም ዓለም መተግበሪያዎች በመጠቀም ሸማቾች ግዢዎችን በስማርት ስልኮቻቸው እንዲፈጽሙ አስችሏል። 

ስለዚህ፤ በዚህ የለውጥ ሒደት ውስጥ የዲጂታል ክፍያ ሥርዐቶችን ምን ምን ጥቅሞች ይሰጡና?

1ኛ. የመሥመር ላይ የክፍያ በኅብረተሰባችን ውስጥ ጥሬ ገንዘብ በመያዝ የሚመጣውን ተጋላጭነት ያቀራል፤ ደንበኞች በአካል ለሚያገኙት አገልግሎቶች የሚጠየቁ የክፍያዎች ወጪን ይቀንሳል፤

2ኛ. እያንዳንዱ ግብይቶች ግልጽነትን እንዲኖረው በማድረግ ቀልጣፋና ምቾት ያለው አገልግሎት መግኘት ያችላል፤ በዚህም የጥሬ ገንዘብ አልባ የክፍያ ሥርዓቶች ክፍያዎችን ቀላልና ምቹ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ያበረታታሉ፤

3ኛ. የጥሬ ገንዘብ አያያዝን በማዘመን ለማውጣትና ለመቁጠር የሚፈጀውን ጊዜና ወጪ ቆጣቢ ናቸው፤ እንዲሁም ገንዘብ እንዳይጭበረበር በማድረግ የበለጠ ደኅንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያስችላሉ፤

4ኛ. በማዕከላዊ ባንክ ቁጥጥር ሥር ያሉ ዲጂታል ምንዛሬዎች የምንዛሪ ተመን አደጋንና የመገበያያ ገንዘብ ተለዋዋጭነትን ያስወግዳሉ፤ ኢኮኖሚያዊ አጋዥ ሆነው ሊያገለግሉ፤ ሕገ ወጥ የጥቁር ኢኮኖሚ እንቅስቃሴንና የታክስ ስወራን ይቀንሳሉ።

5ኛ. ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የበለጠ ቁጥጥር ስለሚያደርግ ወንጀል ይቀንሳል።

6ኛ. የዲጂታል ክፍያዎች ድምበር ተሻጋሪ በመሆናቸው አለም አቀፍ ክፍያዎችን በቀላል መፈጸም ያስችሉናል፤ በተለያዩ አገራት ኢንቨስት በማድረግና ውጪ ምንዛሬን ጤነኛ በማድረግ በኢኮኖሚው ላይ መነቃቃትን ያሳድራሉ፡፡

በአጠቃላይ ለኅብረተሰብና ለመንግሥት፤ ለሸማቾችና ለገዢዎች ትልቅ አንድምታ ይኖራቸዋል ማለት ነው።

በአሁኑ ጊዜም፤ አገራችን ኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ በምታሳየው መነቃቃት በየፋይናንሻል ቴክኖሎጂዎችን የኢ-ኮሜርስ ክፍያዎችን በመጠቀም ላይ ትገኛለች፡፡ ባንካችን አቢሲንያም ግንባር ቀደም በመሆን አቢሲንያ ኢኮሜርስ የክፍያ መንገድ (Abyssinia Ecommerce payment gateway) በተሰኘ የክፍያ አማራጭ ለደንበኞቹ ድረ-ገጽን (website) ወይም መተግበሪያን (App) ቪዛ ወይም ማስተርስ ካርድ በማዋሐድ አየር ላይ ክፍያዎችን መፈጸም የሚያችሉ ሥርዐቶችን ዘርግቶ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

ነጋዴዎች ድረ ገጽን ወይም አፖችን ከአቢሲንያ የክፍያ በር ጋር በማገናኘት በአየር ላይ ከመላው ዓለም ክፍያዎችን መቀበል ወይም መፈጸም ይችላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የ-ኢኮሜርስ ግብይትን የሚያቀላጥፍ ማማ ፔይ (Mama Pay) መተግበሪያን ይፋ አድርጓል፡፡

ውድ ደንበኞቻችን! የምንጊዜ ምርጫችሁ የኾነው ባንካችሁ አቢሲንያ፤ በፋይናንሻል ቴክኖሎጂ (FinTech payment) የሚከሠቱ ዐዳዲስ ውጤቶችን በማስተዋወቅ፤ በዲጂታሉ ዓለም በሚደረገው ጉዞ መንገድ በመኾን ዘወትር ይተጋል፡፡

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

ምኒልክ ብርሃኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button