ባንካችን አቢሲንያ ከቪዛ ጋር በመተባበር በኳታር የሚከናወነውን የ2022 የፊፋ የዓለም ዋንጫን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ገበያ የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ባለቤቶችን እና ተጠቃሚዎችን በካርድ መገበያየትን በማበረታታት የዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶችን ለማሳደግ ያለመ የሽልማት መርሐ-ግበር መዘጋጀቱ ይታወቃል።
የመጀመሪያው ዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ረቡዕ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ/ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ የተከናወነ ሲሆን፣ የመካከለኛው አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ደንበኛ የሆኑት አቶ ሚሊዮን ኢሳያስ ገ/ማርያም በኩፖን ቁጥር FT30144811FG1 የዕጣው አሸናፊ ሆነዋል፡፡
ይህ ታላቅ ሽልማት ደንበኛው ከሚመርጡት አንድ የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ ጋር የመጀመሪያው ዙር የማጣሪያ ጨዋታን ለመመልከት ወደ ኳታር እንዲጓዙ የሚያስችላቸው ሲሆን፣ በተጨማሪም ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል ውስጥ ለሁለት ምሽቶች ማረፊያ፣ የገበያ አበል፣ ከመድረክ ጀርባ በቅርበት ትእይንት የማየት ልምድ እና ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን የማየት እድል ያካተተ ነው።
በዚሁ የፊፋ የዓለም ዋንጫ ኳታር 2022 ዘመቻ በኳታር ተገኝቶ የሁለተኛውን ዙር የምድብ ጨዋታዎችን ለመመልከት የሚያስችውን ሁለተኛውን ሽልማት አካቶ ሌሎች ተጨማሪ በርካታ ሽልማቶች (ባለ 55” ቴሌቪዥኖች፣ ላፕቶፖች፣ ስማርት ስልኮች፣ ፓወር ባንኮች እና ሌሎች አስደሳች ሽልማቶችም) ለአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች የቀረቡ ሲሆን፣ በሽልማት ዕጣ ውስጥ የአቢሲንያ ቪዛ ካርድን በመጠቀም ብዙ ግብይት የፈጸሙ የካርድ ደንበኞች ይካተታሉ።
ለዕድለኛ ደንበኛችንም እንኳን ደስ አለዎት! ከባንካችንም ጋር ስለሚሠሩ እናመሰግናለን ለማለት እንወዳለን፡፡
Leave a Reply