ባንካችን አቢሲንያ የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ

ባንካችን አቢሲንያ የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ

የአቢሲንያ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የስራ አመራር አባላት ባለፉት ስድስት ወራት በባንኩ በተሰሩ ዋና ዋና ክንውኖች ላይ ጥር 23 እና 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሐይሌ ግራንድ ሆቴል በጋራ ግምገማ አካሂደዋል፡፡

በግምገማው ወቅት ከእቅድ አንፃር በዋና ዋና መለኪያዎች ረገድ የተሰሩ ስራዎች በዲስትሪክት ፅ/ቤቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የባንካችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ በአፈጻጸማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዲስትሪክት  ፅ/ቤቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አቶ በቃሉ አሁን በተመዘገበው ውጤት ሳንዘናጋ ባንኩን ወደ ቀደመ ደረጃው ለመመለስና  የገበያ ድርሻውንም ለማሳደግ መላው ሰራተኛ በትጋት እንዲሰራ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን በዲስትሪክት ፅ/ቤቶች የዕለት ተዕለት የስራ እንቅስቃሴም የዋና መ/ቤት የተለያዩ የስራ ክፍሎች ድጋፍ ከምንጊዜውም በላይ ተጠናቀክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ለሁለት ቀናት የቆየው የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ሊበረታቱና ሊሻሻሉ የሚገባቸውን የስራ አፈጻጸሞች በመለየትና የባንኩን የቀሪ በጀት አመት የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።

የግምገማውን መጠናቀቅ ተከትሎም ተሳታፊዎች ባንካችን ከጫካ ቡና ጋር በአጋርነት በዋናው መ/ቤት የከፈተውን ዘመናዊ ከጥሬ ገንዘብና ከወረቀት ንክኪ ነጻ (Cashless and Paperless)የባንክ አገልግሎት በካፌ የሚሰጠውን ማዕከል የጎበኙ ሲሆን ይህም ባንካችን ለቀጣይ 5 አመታት እንዲያገለግል በቀረፀው ስትራቴጂ ላይ ለዲጂታል ቴክኖሎጂ ለሰጠው ትኩረት ጉልህ ማሳይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button