የኮርፖሬት ሰው ኃይል ሠራተኞች በማዕድ ማጋራት ተግባር ላይ ተሣተፉ !!!

የኮርፖሬት ሰው ኃይል ሠራተኞች በማዕድ ማጋራት ተግባር ላይ ተሣተፉ !!!

በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሰማርተው ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ሲያስተዳድሩ የነበሩ ግለሰቡች ዛሬ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባስከተለው መጠነ ሰፊ ችግር ሥራቸውን ትተው በቤት ለማዋል የተገደዱ ወጣቶች፤እናቶችና አባቶችን በሃገር አቀፍ ደረጃ በተያዘው የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ታቅፈው እንዲደገፉ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

የባንካችን የኮርፖሬት የሰው ሀብት ሴክተርም ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል የመረዳዳት መንፈስ፤ በሴክተሩ  ሥር ከሚገኙት የስራ ባለደረቦች(Staffs) ከተሰበሰበው የድጋፍ መዋጮ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ውሰጥ ልዩ መጠሪያው 04/02 በሆነው አካባቢ ነዋሪ ለሆኑ 35( ሰላሳ አምስት) እማወራዎችና አባዎራዎች ፤ግምቱ ሰማኒያ ሺ ብር (80,000) የሚያወጣ የጤፍ፤ የስንዴ፤ የሽሮ እህል፤ ዘይት፤ ፓስታ እና ለጽዳት አገለግሎት የሚውሉ የልብስ እንደሁም የገላ ሣሙና የወረዳው ኃላፊዎች ባዘጋጁት ዝርዝር መሰረት እና በቤተ- ልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ በተካሄደው ፕሮግራም ስጦታው ለተደጋፊዎቹ ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 23/2012 ዓ.ም. ተበርክቷል፡፡