ትላንት፣ ኢትዮጵያ በዓለማችን ቀደምት ሥልጣኔ ከታየባቸው ጥቂት አገራት አንዷ ናት። የሥልጣኔ ምንጯ ደግሞ ትምህርት ነበር፡፡ ከዛሬ ሰባት ሺህ ዓመታት በፊት ትምህርት በጥራት ይሰጥ ስለነበር ከአፍሪካና አውሮፓ እየመጡ ይማሩ ነበር (ካህሳይ ገ/እግዚአብሔር፣ ባህልና ክርስቲያናዊ ትውፊት በኢትዮጵያ፣ 2010)፡፡ በ1906 ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ለዘመናዊ ትምህርት ፈር ቀደዱ (ደስታ በርሀ ስብሃቱ፣ የተውሶ ትምህርት ሥርዓት፣ 2007 )፤ ከእርሳቸው በኋላ ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ ከፍተኛ ደረጃ የትምህርት ተቋማትን በመገንባት ብዙዎች በዚኽ የዕውቀት እልፍኝ ተስተናገዱ። ኢትዮጵያ ግን ከሥልጣኔ ጫፍ ወረደች፡፡
ዛሬ፤ ዓለም የደረሰበት ሥልጣኔ ላይ ለመድረስና ከድኅነት ለመላቀቅ ቁልፉ ትምህርት፡፡ ይኽን የተረዱት ትጉኃኖች በተለያዩ የትምህርት መስክ ራሳቸው በማሳለፍ አንቱታን አትርፈዋል፡፡ ነገር ግን በአኹኑ ጊዜ የትምህርት ክፍያ በከፍተኛ ኹኔታ እየጨመረ በመሔዱ የት ልማር ሳይኾን የትምህርት ክፍያን መቋቋም የሚችል ዐቅም አለኝ? የሚለው እጅግ ያሳስባል። የትምህርት ክፍያዎን እንዴት ሊከፍሉ ይችላሉ?
አኹን፤ ትምህርት የሀብት መለኪያ ኾኗል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን የትምህርት ወጪያችን የሚሸፈነው በቤተሰብ ነው፡፡ እንደቤተሰብ ዐቅም የምንገባበት ትምህርት ቤት ሊለያይና በገንዘብ እጥረት የማንፈልገውን ትምህርት ልንማር እንችላለን፡፡ ዘመኑ ግን ይኽን ስለማይፈቅድ ከማዕቀፉ መውጣት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም አንዱና ዋነኛው መፍትሔው ደግሞ በልዩ ኹኔታ የትምህርት ቁጠባ ሒሳብ መጀመር ነው፡፡
ለምን የትምህርት ቁጠባ ያስፈልጋል?
- ወደ ትምህርት (ኮሌጅ) ለመግባት እንድንወስን፤ ተማሪው እጁ ላይ ገንዘብ ካለ ወደትምህርት ለመግባት በቀላሉ እንዲወስን ያደርገዋል፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ወላጆች ለልጆቻቸው የትምህርት ቤት ክፍያ ሙሉ በሙሉ ለመክፈል በቂ ገንዘብ ላይኖራቸው ይችላልና፡፡
- ብድርን ያስቀራል፤ በትምህርት ቤት ሕይወት ወጪዎች የትምህርት ወርኃዊ ክፍያ ብቻ አይደሉም፡፡ ለኮፒ፣ በት/ቤት ውስጥና ውጪ የሚደረጉ መርሐ ግብራት፣ ከክፍል ጓደኞቻችን ጋር ለመዝናናት አልያም ለመጋበዝ፣ የመጽሔት ክፍያ ወዘተ፡፡ ለተማሪ እነዚኽን ክፍያዎች በቀላሉ መሸፈን ይቸግረዋል፡፡ ያለን አማራጭ ደግሞ አንድ ነው፤ ብድር፡፡ ተማሪዎች ከተለያየ ቦታ ገንዘብ ይበደራሉ፡፡ ብድር ደግሞ በራስ መተማመናችን ይቀንሰዋል፡፡ በተቃራኒ ቁጠባ በራስ መተማመናችን ይጨምራል፡፡
- ዕድሎች እንዳያልፉን፤ የትምህርት ክፍያ በጣም ውድ በመኾኑ በተለይም ስኮላር ሺፕ የማግኘት ዕድል ከገጠመን በገንዘብ ማጣት ምክንያት ይኽ ወርቅ ዕድል እንዳያመልጠን ዐቅም ይፈጥራል፡፡
- የቁጠባ ባህል በማዳበር ወደፊት በሥራ የሚመናገኘውን ገንዘብ በቀላሉ ማስተዳደር እንችላለን፡፡
- በተለይ ቁጠባ እየዳበረ በመጣ ቁጥር ተማሪዎች ገቢያቸውን ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ሥራዎችን መሥራት እንዲችሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ይኽ ደግሞ ከምርቃት በኋላ ሥራ ለመፈለግ የሚባክነውን ጊዜ በማስቀረት ተማሪዎች አነስተኛ ሥራ እንዲጀምሩ ያደርጓቸዋል፡፡
ታዲያ! እነዚኽን ሕልም እንዴት ዕውን ማድረግ ይችላሉ? ነገ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርትዎን የት መማር ይፈልጋሉ? በአገር ውስጥ ወይም በውጪ አገር?
አቢሲንያ ባንክ ለዚኽ ተግባራዊ መልስ ይሰጣል፡፡ ባንካችን የነገ ሕልምዎን ዛሬ ሊጋራ የትምህርት ወጪዎን አኹን መሸፈን የሚያስችሎትን ልዩ የትምህርት ቁጠባ ሒሳብ አዘጋጅቷል። በዚኽ የትምህርት ቁጠባ ሒሳብ ዓለም በደረሰበት የዕውቀት ደረጃ ላይ ደርሰው ተወዳዳሪና ተፈላጊ ኾኖ መውጣት የሚያስችሎትን ሚና ከወዲኹ እንዲወጡ አቅርበናል።
የትምህርት ቁጠባ ሒሳብ ከከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም እስከ መጀመሪያ ዲግሪ ድረስ ትምርታቸውን ለሚከታተሉ ተማሪዎች የተዘጋጀ ልዩ የቁጠባ ሒሳብ ዐይነት ነው፡፡ ከ14-18 ባለው እድሜ ውስጥ የሚገኙ በወላጆቸቸው አሊያም በአሳዳጊዎቻቸው መክፈት ይችላሉ፡፡
የትምህርት የቁጠባ ሒሳብ ገጸ በረከቶች
- ከተለመደው ቁጠባ ሒሳብ ከፍ ያለ የወለድ መጠን ይሰጣል፤
- ደንበኛው የ6 ወር አማካኝ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ከኾነ ለአገር ውስጥ የትምህርት ዕድል የሚኾን የገንዘብ ሽልማት ለሚያሰጥ ውድድር ዕጩ ይኾናሉ፡፡
- የሽልማቱ አሸናፊ የኾኑት ደንበኛ የሽልማቱን ገንዘብ ለትምህርት ዐላማ ማዋል የማይፈልጉ ከኾነና ዐዲስ ሊጀምሩ ያሰቡት መጠነኛ የንግድ ሥራ ካለ፣ ገንዘቡን እንደመነሻ ካፒታል ሊጠቅሙበት ይችላሉ፡፡
- ደንበኞች የውጭ የትምህርት ዕድል የሚያገኙ ከኾነ፤ ባንኩ እንደኹኔታው ለዚህ ዐላማ የሚውል የውጭ ምንዛሪ ሊያመቻች ይችላል፣ ኾኖም ለዚኽ ብቁ የሚኾኑት በትምህርት ሒሳባቸው በአንድ ዓመት ውስጥ የሚኖረው አማካኝ የቀን ተቀማጭ ገንዘብ 50,000 (አምሳ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ መኾን ይኖርበታል፡፡
- የትምህርት ሒሳቡን በመጠቀም የአገር ውስጥ ሐዋላ በሚልኩበት ጊዜ ከክፍያ ነጻ ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡
- ከዚህ ሒሳብ ላይ የሚደረጉ ማንኛውም ቋሚ ትዕዛዞች (standing order) ያለ ክፍያ ይስተናገዳሉ፡፡
አቢሲንያ ሕልምዎን ሊጋራ ዛሬ ላይ ስለ ትምህርትና ስለ ነገ የቀረበ የሁሉም ምርጫ!!
ምኒልክ ብርሃኑ
Leave a Reply