ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈልበት ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • በተ.ቁጥር 1 እና 2 ላይ ያሉት የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 12 ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነዉ፡፡
  • ከተ.ቁጥር 3 እስከ 5 ያሉት ንብረቶች የጨረታ ቦታ አክሱም ከተማ ዉስጥ በሚገኝ የአቢሲንያ ባንክ አክሱም ቅርንጫፍ ዉስጥ ሲሆን ንብረቶቹን ለማየት በስልክ ቁጥር 034-775-23-63 እና 034-775-24-56 መደወል ይቻላል፡፡ 
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-515-11-53 እና 011-515-07-11 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button