ባንካችን አቢሲንያ በወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ማዕከሉ በኩል ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀው ‘‘አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር” ፍፃሜውን አገኘ፡፡

ባንካችን አቢሲንያ በወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ማዕከሉ በኩል ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀው ‘‘አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር” ፍፃሜውን አገኘ፡፡

ባንካችን አቢሲንያ በወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ማዕከሉ በኩል ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀው ‘‘አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር” ችግር ፈቺ የሆኑ በርካታ የውድድር ሐሳቦችን በከፍተኛ ፉክክር ሲያሳትፍ ቆይቶ፤ አሸናፊዎችን በመሸለምና ዕውቅና በመስጠት ፍፃሜውን አገኘ፡፡

በዚህ ውድድር ከቀረቡት የውድድር ሐሳቦች መካከል የተቀመጠውን መለያ መስፈርት ያሟሉ 142 ተወዳዳሪዎች ሐሳቦቻቸው በውድድሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተመርጠው የነበረ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል 126ቱ ተወዳዳሪዎች በግብርና ምርቶች ማሳደጊያ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በዶመስቲክ ትሬድ፣ በሰርቪስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሪሳይክል እና ኢ-ለርኒንግ መስኮች ላይ ምክረ ሐሳቦቻቸውን ማቅረብ ችለዋል፡፡ በውድድሩ ላይ የተለያዩ ምዕራፎችን በብቃት በማለፍ በብዙ መለኪያዎች ነጥረው የወጡ ከ1ኛ እስከ 5ተኛ ደረጃን በማግኘት አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች ባንካችን ከብር 200,000 እስከ ብር 1,000,000 የፕሮጀክት ሐሳባቸውን መሬት እንዲያወርዱ የሚያግዛቸው የሥራ ማስኬጃ ሽልማት ከታላቅ ክብርና ምስጋና ጋር አበርክቶላቸዋል፡፡ 

‘‘አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር” ከባንካችን እሴቶች መካከል አንዱ የሆነው ማኅበራዊ ኃላፊነትን መወጣት በሚለው መርህ መነሻነት የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን እየሰጠ በሚገኝበት ‘‘አቢሲንያ አሚን” በኩል የሚዘጋጅ መሆኑን ተከትሎ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቱን በማስተዋወቅ ረገድም ከፍተኛ ድርሻ ነበረው፡፡ ከመጀመሪያው ዙር የውድድር መድረክ ትምህርት በመውሰድ ሁለተኛው ዙር ከቀደመው በተሻለ መልኩ የተሳካ አፈፃፀም እንዲኖረው ለማስቻል በቂ ዝግጅት በማድረግ፤ በላቀ ስኬት ለማጠናቀቅ ተችሏል፡፡

በመዝጊያ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የብሔራዊ ባንክ የባንኪንግ ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍሬዘር አያሌው በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን፣ በእለቱም ባንካችን ለተለያዩ 6 የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ ለተሰማሩ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች በአጠቃላይ የብር 3 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button