ባንካችን አቢሲንያ የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባን በተመረጡ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 8 ማዕከላት ማለትም አራዳ፣ ገነት፣ ጎፋ፣ ራጉኤል፣ ዶ/ር ካትሪን፣ ላምበረት፣ አፍሪካ ጎዳና እና ለቡ ቅርንጫፎቻችን በይፋ አስጀምሯል፡፡
በመሆኑም ይህን ለአገራችን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው ፕሮጀክት ለማስፈፀም የበኩላችንን አስተዋጽኦ እያበረከትን ስለሆነ የከተማችን ነዋሪዎች ከላይ በተጠቀሱት ቅርንጫፎቻችን እየሄዳችሁ እንድትመዘገቡ ስናሳውቅ በደስታ ነው፡፡

Leave a Reply