አቢሲንያ ባንክ “አቢሲንያ አሚን” በሚል የሰየመው ከወለድ ነፃ አገልግሎቱ፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ ዕቅዶች ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህም አንዱ “አሚን አዋርድ” በሚል መጠሪያ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማትን የሚሰጥበት መርሐግብር ነው፡፡
ት/ቤቶች አምራች እና ብቁ ዜጎችን ከመፍጠር አኳያ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል ይህንን የትምህርት ቤቶችን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም የተማሪዎችን ተነሳሽነት እና ተፎካካሪነትን ለማሳደግ በማሰብ በት/ቤቶች በመገኘት የአሚን አዋርድ የማበረታቻ ሽልማት በማዘጋጀት ሰኔ 26 ቀን 2ዐ14 ዓ.ም. በነጃሺ አካዳሚ በመገኘት የላቀ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የአሚን አዋርድ ሽልማት ስነስርዓት አከናውኗል፡፡
በመርሐግብሩም ላይ የባንኩ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቢዝነስ ዲሬክተር፣ የፋይናንሲንግ ዲሬክተር፣ እና ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች ተገኝተው፣ በትምህርት ቤቱ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ከአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላገኙ 40 /አርባ/ ተማሪዎች በቅደም ተከተል የብር 5,ዐዐዐ፣ 3,ዐዐዐ እና 2,ዐዐዐ የማበረታቻ ሽልማት አበርክተዋል፡፡ በተጨማሪም ከነጃሺ አካዳሚ ጠቅላላ ተማሪዎች ከፍተኛውን ውጤት አስመዝግቦ በአንደኛነት ደረጃ ላጠናቀቀው ተማሪ ከባንካችን የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል፡፡
ዕሤትዎን ያከበረ!
Leave a Reply