አቢሲንያ ባንክ 25ኛውን አመታዊ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤውን ታህሳስ 7 ቀን 2014 ዓ.ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አካሂዷል፡፡ ካለፈው ከተሰበሰበው ገንዘብ 86.6 በመቶ በማሳደግ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን ብር 88.88 ቢሊዮን አደረሰ!
- በ2020/21 በጀት ዓመት ካለፈው በጀት ዓመት ከተሰበሰበው ገንዘብ ሦስት እጥፍ እድገት በማሳየት እጅግ በላቀ አፈጻጸም የብር 41.25 ቢሊዮን ወይም 86.6 በመቶ እድገት በማስመዝገብ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን ከብር 47.63 ቢሊዮን ወደ ብር 88.88 ቢሊዮን ለማድረስ ችሏል፡፡
- አጠቃላይ የሀብት ክምችቱን ባለፈው ዓመት ከነበረው ከብር 56.89 ቢሊዮን በ82.5 በመቶ በማሳደግ ወደ ብር 103.85 ቢሊዮን፣ የካፒታል መጠኑን ደግሞ ከብር 5.68 ቢሊዮን በ52 በመቶ በማሳደግ ወደ ብር 8.65 ቢሊዮን ከፍ ማድረግ የቻለ ሲሆን፣
- ብር 2.05 ቢሊዮን ያልተጣራ ትርፍ አግኝቷል፡፡ ይኸም ባለፈው ዓመት ከተመዘገበው ትርፍ ጋር ሲነጻጸር የ90 በመቶ ከፍተኛ ጭማሪን አሳይቷል፡፡
- የባንኩ አጠቃላይ ሠራተኞች ቁጥር 8,146 ደርሷል፡፡
- 97 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 608 ከፍ ለማድረግ ችሏል፡፡
- የብድርና ቅድመ ክፍያዎች መጠን ብር 76.6 ቢሊዮን ደርሷል፡፡ ይኸም ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ105.9 በመቶ ወይም የብር 39.4 ቢሊዮን የእጥፍ ጭማሪን አሳይቷል፡፡
- የተገኘው የውጭ ምንዛሪ መጠን 753.16 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይኸ አኀዝ ባንካችን ባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አስመዝግቦት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ352.85 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ88 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
- ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተሠራ ላለው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም፣ ለተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች፣ ለመንግሥት ተቋማት እና ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከብር 45.71 ሚሊዮን በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
- የባንካችን የወደ ፊት ዋና መ/ቤት ሕንፃ መገንቢያ ቦታ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ልደታ ክ/ከተማ፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ጎን የሚገኝ ሲሆን፣ አጠቃላይ ስፋቱ 9,763 ካሬ ሜትር ነው፡፡ በዚህ ይዞታ ላይ እስከ 60 ወለል የሚደርስ ሕንፃ ለመገንባት ዓለም ዓቀፍ ተቋራጮች በጨረታ ተወዳድረው አሸናፊው መለየቱ ታውቋል፡፡
Leave a Reply