አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለጂ.ዜድ.ኤ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን በማህበሩ ስም ተመዝግቦ በአማራ ክልላዊ መንግስት በሞጣ ከተማ ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚሆን ጅምር መጋዘን ባለበት ሁኔታና በሚገኝበት ቦታ በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 11,683,575.00 (አስራ አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማንያ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) በ14/11/2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30-5፡30 የተጫራቾች ምዝገባ በማድረግ በግልጽ ጨረታ ንብረቱ ይሸጣል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ በአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ስም በሲፒኦ አሰርተው በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡ የብድር መስፈርት ለሚያሟሉ ተጫራች/ተጫራቾች ብድር እናመቻቻለን፡፡ ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ ዝርዝር መረጃ እሁድ ሰኔ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ታትሞ የወጣውን ሪፖርተር ጋዜጣ መመልከት ይቻላል፡፡ ምስሉን ይመልከቱ
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ
Leave a Reply