አቢሲንያ ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የመጀመሪያ የሆነውን ቨርቹዋል የባንክ ማዕከል Virtual Banking Center አስመረቀ!
ባንካችን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋውቀው ይኽ ማዕከል ፣ የባንክ አሠራርን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እንዲሁም ለተጠቃሚዎችም አዲስ የባንክ ተሞክሮን (Customer Experience) የሚያስተዋውቅ ነው፡፡ ማዕከሉ ለሀገራችን አዲስ በሆነና Interactive Teller Machine (ITM) በተባለ ቴክኖሎጂ፤ አንድ የባንክ ቅርንጫፍ የሚሰጣቸውን በርካታ አገልግሎቶች ከባንካችን የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ጋር የተገናኘ ሆኖ ተጠቃሚዎች በጊዜ ሳይገደቡ ከእሑድ እስከ እሑድ በቀን ለ24 ሰዓታት ልዩ አገልግሎት የሚያገኙበት ነው፡፡
አቢሲንያ ባንክ በዲጂታል ክፍያ ረገድ ግንባር ቀደም ከሆነው ቪዛ (Visa Inc.) ጋር የኤሌክትሮኒክ ንግድን (E-Commerce) ለማቀላጠፍ የሚረዳውን የቪዛ ሳይበር ሶርስ (Visa SyberSource Payment Gateway Technology) የኦንላይን ክፍያ አማራጭ ቴክኖሎጂን በማቅረብ፤ የቅርንጫፍ ተደራሽነቱን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የጀመረውን የቀዳሚነት ጉዞ እነሆ አሁን ደግሞ ይኽን በሀገራችን ከተለመደው የባንክ አገልግሎት ተስፈንጥሮ (Big Leap) የወጣበትን ፈር ቀዳጅ አገልግሎት በአዲሱ ዓመት ለክቡራን ደንበኞቹ አበርክቷል፡፡
ቴክኖሎጂ ወለድ የባንክ አገልግሎቶችን አውራ ከሆነው አቢሲንያ ባንክዎ ያግኙ!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
Leave a Reply